Friday, January 9, 2015

ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጥ።

Major Bekele Gebreyesus



ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጥ።
እስኪ በተጠንቀቅ ልስጥበት ሰላምታ፣
ለቆምሺበት ምድር ላለሽበት ቦታ፣
አንቺ አይደለሽም ወይ የሰራዊቱ እናት የወገን መከታ?
የሀረር ወርቅ አሉሽ ስምሽን አሳንሰው?
የኢትዮጵያ ወርቅ ነሽ ንገሪልን ለሰው፣
ስምሽን ከፍ ያድርጉት መልሰው መላልሰው።
በየመን በረሃ በስቃይ የኖሩ፣ 
በሞትና ህይወት መሃል የነበሩ፣
ዛሬ ነፃ ወጥተው ሃገር የቀየሩ፣
እሰኪ ያንቺን ስራ  ወጥተው ይናገሩ፣
በሻአቢያ እስር ቤት በግፍ የታሰሩ፣
ከ20 አመት በላይ ተረስተው የኖሩ፣
ልፋትሽን ድካምሽን ቀርበው ይመስክሩ።
ሰው ለሰራው ስራ ላረገው ውለታ፣
ማመስገን ይገባል ጥዋትና ማታ፣
እንዴት ዝም ይባላል ጠፋ እንዴ ይሉኝታ?
ለምትወደውና ለምታከበረው፣
የቀድሞው ሰራዊት የምትመኘው፣
ሰላማዊ ህይወት የተሻለ ኑሮ እሰከሚገጥምው፣
ግነባር ቀደም ሁና መታገሉን ነው።
ሰው እንደ ሰው ሆኖ በዚች ምድር ሲኖር፣
ላገር ለወገኑ ለፈፀመው ተግባር፣
ክፉውን በመንቀፍ መልካሙን በማንጠር፣
ሰው በሰራው ስራ ስለ ሁሉም ነገር፣
ማንነቱ ታወቆ ምናለ ቢከበር?
አዎን እናክብራት ይህቺን የኛን ጀግና፣
ምስጋና ይቸራት ዛሬም እነደገና፣
ለሰራችው ተግባር ይገባታልና።

ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጥ::

እስኪ በተጠንቀቅ ልስጥበት ሰላምታ፣
ለቆምሺበት ምድር ላለሽበት ቦታ፣
አንቺ አይደለሽም ወይ የሰራዊቱ እናት የወገን መከታ?
የሀረር ወርቅ አሉሽ ስምሽን አሳንሰው?
የኢትዮጵያ ወርቅ ነሽ ንገሪልን ለሰው፣
ስምሽን ከፍ ያድርጉት መልሰው መላልሰው።
በየመን በረሃ በስቃይ የኖሩ፣ 
በሞትና ህይወት መሃል የነበሩ፣
ዛሬ ነፃ ወጥተው ሃገር የቀየሩ፣
እሰኪ ያንቺን ስራ ወጥተው ይናገሩ፣
በሻአቢያ እስር ቤት በግፍ የታሰሩ፣
ከ20 አመት በላይ ተረስተው የኖሩ፣
ልፋትሽን ድካምሽን ቀርበው ይመስክሩ።
ሰው ለሰራው ስራ ላረገው ውለታ፣
ማመስገን ይገባል ጥዋትና ማታ፣
እንዴት ዝም ይባላል ጠፋ እንዴ ይሉኝታ?
ለምትወደውና ለምታከበረው፣
የቀድሞው ሰራዊት የምትመኘው፣
ሰላማዊ ህይወት የተሻለ ኑሮ እሰከሚገጥምው፣
ግነባር ቀደም ሁና መታገሉን ነው።
ሰው እንደ ሰው ሆኖ በዚች ምድር ሲኖር፣
ላገር ለወገኑ ለፈፀመው ተግባር፣
ክፉውን በመንቀፍ መልካሙን በማንጠር፣
ሰው በሰራው ስራ ስለ ሁሉም ነገር፣
ማንነቱ ታወቆ ምናለ ቢከበር?
አዎን እናክብራት ይህቺን የኛን ጀግና፣
ምስጋና ይቸራት ዛሬም እነደገና፣
ለሰራችው ተግባር ይገባታልና።