Wednesday, April 16, 2014

ይድረስ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል አባላትና ቤተሰቦች።

በመጀመሪያ ይችን ብሎግ በስማችሁ ከፍቼ የበኩሌን የማውቀውን ብቻ በማስረጃ በዚህ መልኩ ሁላችሁም ልታገኙት በምትችሉት መገናኛ እንዳቀርብላችሁ አምላክ ስለፈቀደ ምስጋና ለቸሩ መድሃኒዓለም አቀርባለሁ።

ቀደም ሲል ከሶስት አመት በፊት ከሸኚ ደብዳቤ ጋር በማያያዝ ሊኖራችሁ የሚገባ ወረቀቶች ዳላስ እኔው የምኖርበት ከተማ ውስጥ ላለው ድርጅታችሁ በቦርድ አባሉ ስም አስረክቤ ነበር ግልባጩንም ለኮማንደር ጸጋዪ ውድነህም ልኬ ነበር። በዚህ አጋጣሚ ኮማንደር ጸጋዬ የደረሳቸውን ዶክመንት አስመልክቶ በስልክ ደውለው ስላረጋገጡልኝና ስለሰጡኝም የጨዋ ኢትዮጵያዊ ማሳሰቢያ በጣም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ይችን ብሎግ በስማችሁ ልከፍት ያየሳሳኝ መክኒያት አንዳንድ ችግር ገና ከየመን እስር ቤት ሳትፈቱ ዋሽንግተን ዲሲ ያሉግልለሰቦችም መሃል በጉዳዩ ባለቤትነን በሚል ገንHብ ሲሰበስብ የነበረው አሁንም ስለቀጡሉበት ነው።