Thursday, May 26, 2011

ቁጥር ሁለት።


ኮማንደር ማቲው ለየመን አምባሳደር ዋሽንግተን ዲሲ ምስጋናና ማሳሰቢያ የላኩት።





ከየመን አምባሳደርና ከበታች ካሉት ዲፕሎማቲኮች ጋር ያደረኩት ስብሰባና ውጤቱ ያስደሰታቸው ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ጉዳያችሁንም ሲከታተሉም ስለነበረ በኢዲኤን ላይ ካወጡት እነሆ አንዱን ከዚህ በታች።
ወደ አሚሪካን አገር እንድተገቡ ለማስፈጸም ጉዳያችሁን እንደሚታወቀው ከምኖርበት ዳላስ ቴክሳስ ኮምፑተር ላይ ብቻ ቁጭ ብዬ ሳይሆን በተጨባጭ ከሚመለከተው ጋር ሁሉ በነብስ ስብሰባ በማድረግ ጉዳያችሁን ያቀለሉት ባለስልጣኖች ሁሉ ሚዛኑ ከብዶ እንዲታይቸውና ጉዳያችሁ በስልክ ወይም በኢሜል የሚፈጸም ሳይሆን በነብስ  ከከተማ ወደ ከተማ መብረርን  ይጠይቅ የነበረ እንጂ ማንም ሰው ወንበር ላይ ተቀምጦ ፍትዋችው!እያለ ቢጽፍውጤት የማይሰጥ መሆኑንን ደብዳቤዎች የላኩት ለየመን መንግስት በሚል ያዩት ነውውጤት ባለመገኝቱ ስለሆነም ለሎች ያልሞከሩትን መድሃኒቱ ከየመን መንግስት ጋር በነብስ መነጋገሩ መሆኑ የሚያዋጣውን
 ስለተረዳሁ ከቤቴ ወጥቼ ወደ ድሲ ሄድኩኝ ። ሄውም መጀመሪያ ባጭር ጊዜ ውስጥ ከእስር ቤት ያለምንም እቀባ እንድትለቀቁ፡ ቀጥሎም ወደ አሜሪካን እንድትገቡ በሩን ለማስከፈት። በመሆኑም ስራውና ውጤቱ እየሰመረ ሲመጣ በእግዚአብሄር ፍቃድ ፡ ግለሰቦች እርስ በእርሳቸው መፎካከር ጀመሩ የጉዳዩ ባለቤት ነን እየተባባሉ። ከናካቴው ሪፕርትም ለእነሱ መኝታቸው ላይ ተጋድመው ኢሜል ጽፌነበር ለእከሌ ለእዛኛ ለዚህኛው እያሉ እኔንና ኮማንደር ማቲውንም በቁጥጥራችን ስር ይሁን የሰራችሁት ውጤትም ተባልን በሰው ሰቆቃ ነጋዲዎቹ። ይሄውም እኔ በየቀኑ በኢኢዲኤንዶት ኮም ላይና በዋሽንግተን ሳምንታዊ የአማርኛ ሬዲዮ ስርጭት ላይ በዶክተር ማንከልክሎትና በአቶ ንጉሴ ወልደማሪያም በኩል ጉዳያችሁን አስመልክቶ የተገኘውን ውጤት እገልጽ ስለነበረ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደስ እንዲለው በማሰብ ፡ እነ ጮሌ ከዛ በመውሰድ መጀመርያ በዚህ ቀን ይለቀቃሉ ብዬ ከየመን አምባሳደር ጋር በአደረግነው ስምምነት መሰረት ለህዝብ በማብሰሬና በአሜሪካንም ድምጽ ቀርቤ "ነገ ይፈታሉ" ብዬ በግልጽ ሳቀርብ፡ በዳላስና በዋሽንግተን አማርኛ የሬዲዮ ዝግጅት ላይ ሳይቀር የውሸት ጉዳያችሁን አስፈጻሚዎች ሲያስተጋቡ ተሰማ።
በተለይ የመን ለሚገኘው በጊዜው አሁን አሜሪካን ያለው ግለሰብ "ጉዳያችህን ወደ አሜሪካን እንደትመጡ ከዛ አገር ተላቃችሁ በማሰብ ለአሜሪካን መንግስት እንዲቀበላችሁ በስዴተኝነት ማመልከቻ አስገብቼ ከዩኤን ኤች ሲአርም ጋር እየተነጋገርኩኝ ነው ለሰባት መቶ ስዴተኞች ብዬ ነው የጠየኩት ስለዚህ ስንት እንደሆናችህ በስም ሳይሆን በቁጥር አስረዳኝ በኢሜል ደውዬ በስልክ እነግረዋለሁ። ግለሰቡ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚኖር ግለሰብ ለካስ ይነግረው ኖሮ ምን አደረሰችላችሁ እያለ በጠየቀው ቁጥር ያልታሰበ ችግር ይፈጠራል።   ትልቁ ችግር የተጀመረው ከአሜሪካን መንግስት እናንተን ብቻ አስመልክቶ ወደ የመን በመሄድ ብሎም ሌላ ከአሜሪካን ውጭ ያለ ኤጀንት ጭምር የመን ድረስ ሄደው ጉዳያችሁን እንዲያከናውኑ መፈቀዱን አብረውኝ በጉዳዩ ሃላፊነት ይሰሩ የነበሩት ባለስልጣን እንዳበሰሩኝ የደስታ መግለጫ ስለጉዳያችሁ ሲወሳበት በነበረው EEDN.COM ላይ በማውጣቴ ለካስ ዲሲ ውስጥ ግለሰቦች እየተፎካከሩበት በሬዲዮና
 በዌብ ሳይትም ሳይቅቀ በየከተማው ዳላስ ቴክሳስ ጭምር" እሁድ ቀን ይገባሉ ሁሉም ባንድ ቀን በአንድ ላይ ዋሽንግተን ዲሲ፡ አፓርትመንትም አሰራንላቸው!" በሚል ጭምር የፈጠራ ወሬ ለግል ጥቅም መሰብሰቢያ ይለፈፋል። የትግሬ ነጻ አውጪ መንግስት ይችን ሲሰማ እዛው ዲሲ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ቀደም ሲል የየመን አምባሳደር ከእኔ ጋር ያደረጉትን ስብሰባና ያለምንም የመብት ግደባ በመለቀቃችሁ መክኒያት የየመን መንግስት እንዳይተባበረኝ በእኔ ላይ ያቀረበውን ክስ ቀጥሎም ለአሜሪካን መንግስትም አቀረበ ተቀባይነት እንዳይኖረኝና እናንተም ወደ ኢትዮጵያ እንድትመለሱ ጥያቄ አቀረበ። ጉዳያችሁ አደጋ ላይ እንደወደቀ ስረዳ ከሌሎች ጋር መነጋገሩን ትቼ ከኮማንደር ማቲው ጋር ብቻ በመስራት ኮማንደር እስከመጨረሻም ምጽዋም ስለነበሩም አስፈላጊውን ማስረጃም ይሁን ማንኛውንም የአሜሪካን መንግስት የሚጠይቀውን እንደአስፈላጊነቱ እሳቸው እንዲያቀርቡ ተስማምተን፡ እሳቸውንም ጉዳያችሁን ለያዘው መስሪያ ቤት ባለስልጣኖች ማንነታቸውን በማስተዋወቅ ከሳቸው ሌላ ማንም ከማን ጋር እንደምሰራ ሳያውቅ ጉዳያችሁ እግቡ ሊደርስ ችልዋል።


ኮማንደር ማቲው መኮንን ከላይ በገለጽኩት መክኒያቶች ጉዳያችሁ እንዳይበላሽ ከዚህ በታች ያለውን መግለጫና ማረምያ በጊዜው በEEDN.COM ላይ በይፋ ያወጡትን የታገሉትን እነሆ። 






           




አምላኬ ምስጋና ይግባህ ለዚች ቀን አሜን።

ይቀጥላል።


Monday, May 2, 2011

ከየሐረርወርቅ ጋሻው፡ ይድረስ ለባሕር ሃይሉ ጀግና! ቁጥር አንድ።

ይድረስ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል ባልደረቦች፡ ሴቪሎችና መላው ቤተሰባችሁ። አምላክ ፍቃዱ ሆኖ ከየመን ከአስራ ሶስት አመት ስቃይ በሁዋላ የሰላምን እንቅልፍ በአሜሪካን ላጎናጸፋችሁ ለአምላክ በተለመደው የየቀኑና ምሽቱ ተግባሬ አድርጌ በምኖረው ስራአት እግሩ ስር ተደፍቼ አመሰግነዋለሁ ደግሜ ደጋግሜ እስኪጠራኝ ወደ ዘለአለም ቤቴ። እናንተም እንደዚሁ እንደምታመስገኑትና ምስጋና ለክብሩና ለደግነቱ እንደምታቀርቡ በየቀኑ አልጠራጠርም።

በሚቀጥለው ገለጻ ይኖረኛል። ሆኖም  ወደ ፊትም የምጽፈው ማጠቃለያ ውስጥ ከሚገኙት ሰዎች መሃል በኖሩም ለዛሬ ይችን ብሎግ ለመክፈት ክብራቸውን ከፍ አድርጌ ኮማንደር ማቲው ተፈሪንና ነብሱን ይማረውና የመቶ አለቃ ሳሙኤል ጥሩነህን ትልቅ አስተዋጽዎ አብርውኝ በመስራት ስላደረጉት ትብብር ሳላመስግን ወደ ሚቀጥለው ልገባ ሕሌናዬ ስለማይፈቅድልኝ፡ ስለእነዚህ ሁለት ወንድሞቼ ባጭሩ ለዛሬ ልጠቅስ እወዳለሁ። ይሄውም የመቶ አለቃ ሳሙኤል ኑሮው በስዊድን ስቶኮልም የነበረ ከኮማንደር ማቲው መኮንን ተፈሪ ጋር ብስልክ እንድገናኝ በማድረጉ ትልቅ ስራ ሊሰራ ተችልዋል። ኮማንደር ማቲው መኮንን የጉዳያችሁ አዳራሽና አባት ብሎም ማሕደሩም ናቸው።

NEWS REPORT

UNHCR officials in US are surprised.
By Yeharerwerk Gashaw
April 10, 2004


WASHINGTON DC - The “Ethiopian Refugees' In Yemen Advocate Group USA” met with the UNHCR officials here in the United States, in order to address the Ethiopian refugees' issue in Yemen. The UNHCR headquarters is based in Washington D.C. and works closely with the United States Government.

Among the officials at the meeting was Mr. Larry Yungk, a Senior Resettlement Counselor. According to Mr. Yungk, he used to work in Yemen at UNHCR and he met the former Ethiopian Naval members political refugees while he was in Yemen at the beginning of their arrival.
Mr. Yungk and all the officials were surprised to hear from this reporter about the situation of the refugees in Yemen that was presented with evidence (documents). All told me that usually they get information about refugees from every part of the world, but the Ethiopian naval members in Yemen.
Yungk said it has been two years since he heard about the Ethiopian refugees in Yemen. After a long meeting, all made a decision to take care of the situation in order to end the problem as soon as we end the meeting , by communicating immediately (April 5) with the UNHCR in Geneva, UNHCR in Yemen, and with the Yemeni Government. The Yemen Embassy is willing to work with the Washington UNHCR, it was learned.

ETHIOMEDIA.COM - ETHIOPIA'S PREMIER NEWS AND VIEWS WEBSITE
© COPYRIGHT 20001-2003 ETHIOMEDIA.COM. EMAIL: webmaster@ethiomedia.com



 
ከለንደን የባህር ሃይል ባልደረባ ብርሃኑ መለስ ዘውዴ (BMZ) ከዚህ በታች የላኩልኝ በኤሚል ትልቅ ሚና የተጫወተ ማስረጃ ሲሆን እንዴት አድርጌ መረጃውን ለተለያየ ቦታ መሰረት አድርጌ በመውስድ ካዘለው ውስጥ በሙሉ እንደተጠቀምኩበት ወደ ፊት ታዩታላችሁ ማለት ነው። ይሄ ደብዳቤ ለፕሬዘደንት ጆርጅ ደብል ዩ ቡሽም በእጅ ከተሰጠው አንዱ ሲሆን የዚህ ሁለት ገጽ ሚና በሆም ላንድ ሴኩሪቲም ጀግንነት ስርትዋል።
ለአቶ ብርሃኑ መለስ ዘውዴ እድሜ ከጤናጋር ይጨምርላቸው እግዚአብሄር።



ይቀጥላል!

አምላካችን ለዚች መለክት እድል ስለሰጠህኝ አመሰግንሃለሁ አሜን።